
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከል (CPD Center) ዋና ዓላማ የጤና ባለሙያዎችን ክሊኒካዊ ክህሎት እና ዘመናዊ የሕክምና እውቀት በየጊዜው በማጎልበት የማህበረሰባችን የጤና አገልግሎት ጥራት ማሳደግ ነው። ማዕከሉ “የጤና ባለሙያዎችን ማብቃት፤ የህክምና አገልግሎትን ማሳደግ” የሚለውን ራዕይ በመሰነቅ በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎች የንድፈ-ሀሳብ እውቀታቸውን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር የሚያስተሳስሩበትን ምቹ የስልጠና ድጋፍ ይዘረጋል። ይህ ዓላማ ባለሙያዎችን ብቁ ከማድረግ ባለፈ፤ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን በዕውቀትና በጥራት ለመሙላት ታስቦ የተነደፈ ነው።
ይህንን ዓላማ ለማሳካት ማዕከሉ አራት ዋና ዋና አገልግሎቶችን በግንባር ቀደምትነት ያከናውናል። የመጀመሪያው በአካልና በኦንላይን የሚሰጡ ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎች ሲሆኑ፣ እነዚህም በክህሎት ላብራቶሪዎች (Simulation Labs) የተደገፉ ናቸው። ሁለተኛው የጤና ምርምሮችን ማካሄድ እና ማሰራጨት ሲሆን፣ ሦስተኛው ደግሞ የቨርቹዋል ዌብናሮችን እና ራስን በራስ የማስተማሪያ የዲጂታል ሞጁሎችን (iHRIS Integration) በስፋት መተግበር ነው። አራተኛው እና ወሳኙ ተግባር ደግሞ ባለሙያዎች የሚያገኟቸውን የCPD የትምህርት ነጥቦች (CEUs) በቀጥታ ከሙያ ፍቃድ እድሳት ሲስተም ጋር በማገናኘት የመያ ፈቃድ እድሳትን ማቀላጠፍ ነው።
በተጨማሪም የማዕከሉ የሥራ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ የብቃት ማሻሻያ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ከምርምርና ስልጠና ባሻገር ክሊኒካዊ ውይይቶች፣ የሕክምና ጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራዎች፣ ሙያዊ የምክር ድጋፎች (Mentorship) እና የጤና አመራር ስልጠናዎች በማዕከሉ ውስጥ ይሰጣሉ። ማዕከሉ እነዚህን ስልታዊ ስራዎች በማቀናጀት ጥራት ያለው ትምህርት፣ የሙያ ልቀትን እና የተሻለ የጤና ውጤትን በተግባር ያረጋግጣል።
ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም
የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
For the latest updates:
🌐 Website: http://www.dku.edu.et
📘 Facebook: https://www.facebook.com/Debarkuniversityandcollegeofficial
🐦 Twitter: https://twitter.com/DebarkUniETH
📲 Telegram: https://t.me/+Ed4_Lp3bywo4MzI0
📹 YouTube: https://www.youtube.com




