ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሥራዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመደገፍ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞቹ የኦንላይንና ቅይጥ ትምህርት ትግበራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ። ለዚህም የመምህራን የዲጂታል ትምህርት ይዘት የማዘጋጀትና የማስተማር አቅም ለማሳደግ የሚያስችል በኦንላይንና ቅይጥ ኮርስ ቀረጻ ላይ ያተኮረ የምክክር ወርክሾፕ ጥቅምት 13/2019 ዓ/ም አካሂዷል። …
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሀብትና ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የለማ የሰብል ማሳ የጉብኝት መርሃ ግብር ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል። በጉብኝቱ ወቅት የምርጥ ዘር ብዜትና እና ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የባቄላ እና የስንዴ (አሊ ዶሮ)፣ …
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተያዘው ወር መጨረሻ ተማሪዎችን ለመቀበል ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ፣ በበጀት ዓመቱ የመማር-ማስተማር ሥራ አጀማመር ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ያለመ ውይይት ከመምህራን ጋር ትላንት መስከረም 13/2019 ዓ.ም አካሂዷል። የተቋሙን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ግልጽ በማድረግ የበጀት ዓመቱን የመማር-ማስተማር፣ የምርምር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና …
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሆን ሁለንተናዊ የአይነት ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ በዩኒቨርሲቲው የተመረተ የምግብ እህል እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ኢንተርፕራይዝ ማተሚያ ቤት የተዘጋጁ የተማሪ ደብተሮችን ያካተተ ነው። በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር መ/ር ጌታቸው …
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየውን ዘመናዊ የማህበረሰብ የመጀመሪያ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ዛሬ መስከረም 11/2019 ዓ.ም በይፋ ሥራ አስጀምሯል። በቦታው ተገኝተው የመማር ማስተማር ሂደቱን እና አጠቃላይ ሁኔታውን የተከታተሉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ል ፕሬዚዳንት …
የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስዳችሁ የመግቢያ ነጥብ ያሟላችሁ ውድ ተማሪዎች፣ የአካዳሚክና የሙያ ጉዟችሁን በጥራት ለመጀመር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ! 🏔️ ዩኒቨርሲቲያችን በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ ተማሪን ማዕከል ያደረገ የመማርና የማስተማር ሥርዓት ለመገንባት በሰፊው እየሰራ ይገኛል። …
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዞች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 66 እና በኢንተርፕራይዞች ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 450/2012 መሠረት ያቋቋመው “ራስ ደጀን ንግድና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ” ከምስረታ ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቶ በአሁኑ ወቅት ሙሉ …








