
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይንና ቅይጥ ትምህርት (Online and Hybrid Course) ትግበራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ።
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሥራዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመደገፍ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞቹ የኦንላይንና ቅይጥ ትምህርት ትግበራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ። ለዚህም የመምህራን የዲጂታል ትምህርት ይዘት የማዘጋጀትና የማስተማር አቅም ለማሳደግ የሚያስችል በኦንላይንና ቅይጥ ኮርስ ቀረጻ ላይ ያተኮረ የምክክር ወርክሾፕ ጥቅምት 13/2019 ዓ/ም አካሂዷል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ በወርክሾፕ የመክፈቻ ንግግራቸው፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን እድገት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ በተለይም በመማር ማስተማሩ እየፈጠረ ላለው ተፅዕኖ ምላሽ ለመስጠት ዩኒቨርሲቲያችን የዲጂታልና የኢ-ለርኒንግ ሥርዓት የሽግግር ትግበራን በቁርጠኝነት መምራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበው፤ ዩኒቨርስቲው ለዚህ ወሳኝ ተቋማዊ ስትራቴጂክ ጉዳይ አስፈላጊው የሰው ሃይል የአቅም ግንባታ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው የኦንላይን ትምህርት ትግበራን በሁሉም ፕሮግራሞች በማስፋፋት፤ የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል ።
የኢ-ለርኒንግ ዳይሬክተሩ መምህር ሀብታሙ ታሪኩ በበኩላቸው፣ ወርክሾፑ መምህራን የዲጂታል መማሪያ ማኔጅመንት ሥርዓትን (LMS) በመጠቀም ዲጂታል ኮርሶችን በብቃት እንዲያዘጋጁና እንዲያስተዳድሩ ለማስቻል የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። የኢ-ለርኒንግ ማዕከሉም ቀጣይነት ያለው የቴክኒክ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አንተነህ አገዘው በማጠቃለያ ንግግራቸው፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እውቀትን ከማስተላለፍ ባለፈ እውቀት የሚተላለፍበትን ዘዴ ማዘመን እንዳለባቸው አስገንዝበው ፤የኦንላይንና ቅይጥ ትምህርት መምህራን ጥራት ያላቸውን ዲጂታል ይዘቶች እንዲያዘጋጁ፣ የተማሪዎችን ተሳትፎ እንዲያሳድጉና የትምህርት ጥራትን እንዲያሻሽሉ እንደሚያግዝ ጠቁመዋል። የስልጠናው ውጤት በተግባር እንዲተረጎምም ተቋማዊ ቁርጠኝነት፣ ትብብርና ቀጣይነት ያለው ክትትል አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።
ዩኒቨርሲቲው በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የኦንላይንና ቅይጥ ትምህርት ትግበራን በማጠናከር፤ የዲጂታል ትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማሳደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።
#ደባርቅዩኒቨርሲቲ #የኦንላይንትምህርት #የቅይጥትምህርት #ዲጂታልትራንስፎርሜሽን #ኢለርኒንግ #ከፍተኛትምህርት
ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ
For the latest updates:
🌐 Website: http://www.dku.edu.et
📘 Facebook: https://www.facebook.com/Debarkuniversityandcollegeofficial
🐦 Twitter: https://twitter.com/DebarkUniETH
📲 Telegram: https://t.me/+Ed4_Lp3bywo4MzI0
📹 YouTube: https://www.youtube.com



