
በዩኒቨርሲቲያችን ግቢ ውስጥ የለማ የሰብል ማሳ የጉብኝት መርሃ ግብር ተካሄደ።
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሀብትና ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የለማ የሰብል ማሳ የጉብኝት መርሃ ግብር ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል።
በጉብኝቱ ወቅት የምርጥ ዘር ብዜትና እና ለምግብ ፍጆታ አገልግሎት የሚውሉ የባቄላ እና የስንዴ (አሊ ዶሮ)፣ ድንች (የበለጠ፣ ጉደኔ እና ስኳሬ) ተጎብኝተዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የሃብትና ገቢ ማመንጫ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ባዬ ለጎብኝዎች እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው በዳባትና በደባርቅ ከ44 ሄክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የስንዴ፣ ባቄላ፣ ድንች እና አብሽ በማልማት ላይ እንደሚገኙ አስታውሰው፤ የግብርና ልማት ተግባር ዋና ዓላማ ምርቱን ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የውስጥ ገቢን ማሳደግ እንደሆነ ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በበኩላቸው የተከናወነውን የልማት እንቅስቃሴ ካዩ በኋላ ስራውን የበለጠ የሚያጠናክሩ ገንቢ አስተያየቶችና ምክረ-ሀሳቦችን አቅርበዋል። አቶ ዮሐንስ ለተሰጡት አስተያየቶችና ለታየው አጋርነት ምስጋና አቅርበው፤ የተሰጡ ግብረ-መልሶች በመጠቀም በቀጣይም የምርታማነት ስራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ጥቅምት 8/2019 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
For the latest updates:
🌐 Website: http://www.dku.edu.et
📘 Facebook: https://www.facebook.com/Debarkuniversityandcollegeofficial
🐦 Twitter: https://twitter.com/DebarkUniETH
📲 Telegram: https://t.me/+Ed4_Lp3bywo4MzI0
📹 YouTube: https://www.youtube.com



