አማርኛ ዜናዎች

  • Home
  • አማርኛ ዜናዎች

በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ወርክሾፕ ተካሄደ

  • Posted by admin
  • Date ሚያዝያ 9, 2025

በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ወርክሾፕ ተካሄደ

በደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ “1st Annual Science and Technology Workshop” መጋቢት 30/2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ከደባርቅ ከተማ አስተዳደርና ከሰሜን ጎንደር ዞን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በወርክሾፑ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የአ/ም/ቴክ/ሽግግርና ማ/አገልግሎት ም/ል ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት ዶ/ር መዝገቡ ማንመክቶ ወርክሾፑ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከመማር ማስተማሩ በተጓዳኝ በመምህራን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለማሳየት ያለመ መሆኑን አስታውሰው፤ በሌሎች ኮሌጆች በተመሳሳይ የሚሰሩ ስራዎች ለእይታ መቅረብ እንዳለባቸው በአፅኖት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በዋናነት ባዘጋጀው በዚህ ዓመታዊ ወርክሾፕ በኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል መምህራን የተፈጥሮ ግብአቶችን በመጠቀም የተዘጋጁ ለንፅህና መጠበቂያ የሚውሉ የተለያዩ ሳሙናዎች፣ሳኒታይዘሮች እና ሽቶዎች እንዲሁም በኤክሲሬይ ምስል ኒሞኒያ በሽታን ለማረጋገጥ የሚያግዝ በኮምፒዩተር ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህራን የበለፀገ ሞባይል አፕሊኬሽን ሶፍት ዌር ለእይታ ቀርበዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ከሁለቱም ትምህርት ክፍሎች በወርክ ሾፑ የቀረቡ ስራዎችን ሂደት የሚገልፁ ጽሁፎች ቀርበዋል፤ፓናል ውይይትም ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ መጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ በሂደቱ የተሳተፉ አካላትን በማመስገን፤ በወርክሾፑ ለእይታ የቀረቡ ምርቶችን ጥራት እና ደረጃ የበለጠ በማሻሻልና በማስፋት ምርቶቹን ከማስተማሪያነት ባለፈ ወደ ገበያ ለማቅረብ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል፡፡

መጋቢት 30/2017 ዓ.ም

የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

  • Share:
admin

Previous post

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ
ሚያዝያ 9, 2025

Next post

የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ስራ አፈፃፀም ተገመገመ
ሚያዝያ 19, 2025

You may also like

🎓 የስኬት ጉዟችሁን በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጀምሩ!
መስከረም 15, 2026

የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስዳችሁ የመግቢያ ነጥብ ያሟላችሁ ውድ ተማሪዎች፣ የአካዳሚክና የሙያ ጉዟችሁን በጥራት ለመጀመር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ! 🏔️ ዩኒቨርሲቲያችን በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ ተማሪን ማዕከል ያደረገ የመማርና የማስተማር ሥርዓት ለመገንባት በሰፊው እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም …

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ
መስከረም 15, 2026

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከል (CPD Center) ዋና ዓላማ የጤና ባለሙያዎችን ክሊኒካዊ ክህሎት እና ዘመናዊ የሕክምና እውቀት በየጊዜው በማጎልበት የማህበረሰባችን የጤና አገልግሎት …

dku_204
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎቹን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።
ሰኔ 28, 2026

Latest Posts

🎓 የስኬት ጉዟችሁን በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጀምሩ!
መስከረም 15, 2026
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ
መስከረም 15, 2026
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎቹን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።
ሰኔ 28, 2026
መስከረም 2026
ሰ ማ ረ ሐ ዓ ቅ እ
 123456
78910111213
14151617181920
21222324252627
282930  
« ሰኔ    

[elementor-template id=”16477″]