
ከዳሎል እስከ ራስ ደጀን ትብብር
“ከዳሎል እስከ ራስ ደጀን ትብብር” በሚል መሪ ቃል በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ እና በሰመራ ዩኒቨርሲቲ መካከል የትብብር ስምምነት ተፈረመ
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የልህቀት ማዕከላት ተኮር የሆነ ስትራቴጅካዊ ትብብር ለማድረግና በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም ተፈራረመ።
”ከዳሎል እስከ ራስ ደጀን ትብብር” በሚል መሪ ቃል የተፈረመው ይህ ስምምነት የተካሄደው በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ የተመራ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የልዑካን ቡድን የሰመራ ዩኒቨርስቲን ለመጎብኘት በተገኙበት በሰመራ ዩኒቨርስቲ መሆኑ ታውቋል።ስምምነቱ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በጤና፣ በዘላቂ የማዕድን ልማት በጋራ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ የመምህራንና ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሮችና ሌሎች የአቅም ማጎልበቻ ተግባራትን በጋራ ለመስራት እንደሚያግዝ ተገልጿል።
ስምምነቱ የአቻ ዩኒቨርሲቲዎች የትብብር መንፈስን ለማጠናከርና ተቋማት በሀገራዊ የእድገትና ልማት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የመስራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ለማስገንዘብ እንደሚረዳ ይጠበቃል ።
ጥቅምት 4/2018 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ



