
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የSTEM ማዕከል በ10ኛው ብሔራዊ የሳይንስና ኢንጂነሪንግ ውድድር ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ (STEM) ማዕከል ከህዳር 1-4/2018 ዓ.ም በተካሄደው 10ኛው ብሔራዊ የሳይንስ እና የኢንጂነሪንግ
ውድድር ሶስተኛ ደረጃን መያዙ ታውቋል።ውድድሩን ትምህርት ሚኒስቴር ከቁልፍ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በውድድሩ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የSTEM ማዕከላት የተሰባሰቡት እንደነበር ታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው የSTEM ማዕከል አስተባባሪ መ/ር ፍቃዱ ታርቆ እንዳስታወቁት ከማዕከላችን አጠቃላይ ስኬት በተጨማሪ፣ የDKU STEM ማዕከል ተማሪ መሳፍንት አስረስ ከተወዳደሪ ተማሪዎች ሁሉ በግለሰብ ሁለተኛ ደረጃን በማስመዝገብ ልዩ ተሰጥኦውን እና የፈጠራ ስራውን አሳይቷል።ተማሪ መሳፍንት በኢዱስትሪያልና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተወዳደረ ሲሆን በገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ ተማሪዎች ሁሉን አገልግሎት የሚሰጥ ሶላር ኢነርጅ የተገጠመለት ዘመናዊ ቦርሳ ስራ አቅርቧል።ስኬቱ በማዕከላችን ውስጥ የዳበሩ ጠንካራ የቴክኒክ ክህሎቶች እና የችግር አፈታት ችሎታዎችን ያንፀባርቃል።
ሌሎች የማዕከላችን ተወካዮች – ተማሪ መኳንንት ፈንታሁን እና ተማሪ ገብረአረጋዊ በኢዱስትሪያልና ማኑፋክቸሪንግ እና በሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ዘርፍ – አስደናቂ የፈጠራ፣ የትንታኔ ጥንካሬ እና የላቀ የቴክኒክ እውቀት የሚያሳዩ ድንቅ ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል። ስራቸው የDKU STEM ማዕከልን ቁርጠኝነት እና የትብብር የፈጠራ ባህል ያሳያል።
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለመሳፍንት፣ ለመኳንንት እና ለገብረአረጋዊ ላሳዩት አስደናቂ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ይላል። የእነሱ ስኬት በSTEM ማዕከል እና ሌሎች ተማሪዎችን ለሳይንስ እና ቴክኖሎጆ ፈጠራ እንደሚያነሳሳ ይታወቃል ።



