
የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ተማሪዎች የመጀመሪያውን የቱሪዝምና ሆቴል ሳምንት እያካሄዱ ነው
በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል የ4ኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ለኢቨንት ማኔጅመንት ኮርስ ማሟያ ዓላማን ያያዘ የቱሪዝምና ሆቴል ሳምንት ዝግጅት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ተማሪዎች በተገኙበት “ዋልያን በትኩረት እንጠብቅ” በሚል መሪ ቃል ግንቦት 30/2017 ዓ.ም መካሄድ ጀምሯል።



በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካ/ም/ቴክ/ሽግ/ማ/አገ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋሻው ግስሙ ቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት የዩኒቨርሲቲው አንዱ የልህቀት ማዕከል መሆኑን አውስተው “ዋልያን በትኩረት እንጠብቅ” በሚል መሪ ቃል የቱሪዝምና ሆቴል ሳምንትን ማክበር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበረሰባዊና ትምህርታዊ ፋይዳው ላቅ ያለ ነው ብለዋል። በቀጣይ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ሰፊ የቱሪዝም ንቅናቄ እና የካባቢ ጥብቃ ስራ እንደሚሰራ ዶ/ር ጋሻው አክለው ገልፀዋል።
ከግንቦት 30- ሰኔ 1/2017 ዓ.ም የሚካሄደው
የቱሪዝምና ሆቴል ሳምንት ዝግጅት የአካባቢውን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ፀጋ የሚቃኝ (poster presentation)፣የፎቶ አውደ ርዕይ፣የምግብ ዝግጅት፣ የጥያቄና መልስ ውድድርና የቁንጅና ውድድር፣ የግጥም እና ሙዚቃ ክንውኖችን እንዳካተተ ለመረዳት ተችሏል።
ሰኔ 1/2017 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ