
የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን የደባርቅ ዩኒቨርሲቲን የቁልፍ አፈፃፀም አመላካቾች(KPI) ትግበራ ገመገመ
የትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቁልፍ አመላካቾች እና ተግባራት አፈጻጸም እና ክትትል ድጋፍ ቡድን በቁልፍ አፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) ትግበራ ላይ ከዩነቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ጋር ከሚያዝያ 17-20/2017 ዓ.ም የቆየ ተከታታይ ውይይት እና ግምገማ በቨርቹዋል አካሂዷል፡፡


በዶ/ር እዮብ አየነው የተመራው የሱፐርቪዥን ቡድን በየዘርፉ በተዘጋጁት የድጋፍና ክትትል ቸክሊስቶች መነሻነት ከተማሪ ተወካዮች፣ከአስተደደር ሰራተኛ ተወካዮች፣ከመምህራን ተወካዮች እና ስራ አስፈፃሚዎች፣ዳይሬክተሮች፣ትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ከአስተባባሪዎች እንዲሁም ከቡድን መሪዎች ጋር ወይይት በማድረግ የቁልፍ አፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) ትግበራን ገምግሟል።

በየመርሃ-ግብር ሂደቱ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ወሳኝነት ያላቸው አስተያየቶችም ተሰጥተዋል፡፡ በየሂደቱ መጨረሻም ከተነሱ ጥያቄዎች የተወሰኑት በድጋፍና ክትትል ቡድኑ አባላት ምላሽ/ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና በትምህርት ሚኒስትር ማኔጅመንት አባላት እንዲመለሱ ተለይተው ተይዘዋል፡፡


በመጨረሻም ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስትር ሱፐርቪዥን ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይትና ግምገማ ያካሄደ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ሚያዝያ 20/2017ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ