
የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር ሽማግሌዎች የገና በዓልን ከዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች ጋር አከበሩ
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎች በተዘጋጀው የምሳ መርሃ-ግብር ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንቶች ጨምሮ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ የ7ቱ ከዘራ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት አመራሮችና ስራ አስፈፃሚዎች በተማሪዎች የምግብ አዳራሽ ተገኝተው ከተማሪዎች ጋር በዓሉን አክብረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የ7ቱ ከዘራ የሀገር ሽማግሌዎች ተማሪዎችን እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የጤና ፣ የሰላም ፣ የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል::
ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም
ደባርቅ ዩኒቨርስቲ ።


