
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመረቀ
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛው በቅድመ ምረቃ መርሃ-ግብር ለስድስተኛ ጊዜ በድህረ-በምረቃ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የካቲት 29/2017 ዓ.ም በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል፡፡ በቅድመ ምረቃ መርሃ-ግብር በአራት ኮሌጆች በ24 ትምህርት ክፍሎች 410፣ በድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር በቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት 6፣ በPGDT 115፣ በHDP 29 በአጠቃላይ 560 ተማሪዎችን ማስመረቁ ታውቋል፡፡
በምረቃው ስነ-ስርዓት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ፣የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ አማካሪ አቶ ግዛት አብዩ፣ የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ማህበር አባል፣ሲኔር ተመራማሪ እና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር አለማየሁ ቢሻው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ ዲያቆን ሸጋው ውቤ እንዲሁም በጀርመን ሀገር የጤና ሳይንስ ተመራማሪ ዶ/ር አደራጀው ዋካ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል፡፡





በዋልያ ሙዚቃ ባንድ የደመቀው የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንቶች እና የክብር እንግዶች ዕለቱን የተመለከቱ ንግግሮች፣ በዋና ሪጅስትራር ጽ/ቤት አጭር ሪፖርት፣ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሜዳሊያ እና የዋንጫ ሽልማቶች የታጀበ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡
በምረቃ መርሃ-ግብሩ መጨረሻ ማርች ኤይት(March 8 ) አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ተመራቂ ተማሪዎች እና እንግዶች የደም ልገሳ መርሃ- ግብር አካሂደዋል::

የካቲት 29/2017 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ