
በደባርቅ እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ፡፡
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያላቸውን መልካም ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ዋና ዓላማው ያደረገ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ህዳር 13/2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡
በሁለቱም የዩኒቨርሲቲ ቡድኖች መካከል የተካሄደው ጨዋታ ተመልካችችንም ሆነ ተጫዋቾችን ያዝናና እና ጥሩ ስሜትን የፈጠረ ሲሆን፣ ጨዋታው 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
በመጨረሻም የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ቡድንን የመሩት አስተባባሪዎች ለተደረገላቸው አቀባበልና የሽኝኝት ፕሮግራም አመስግነው፣ የተቋማቱን መልካም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደዚህ አይነትና መሰል ስፖርታዊ ጨዋታዎችም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ሊካሄድ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
ጥቅምት 16/2018
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

