
ለደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ አመራሮች የስትራቴጅክ እቅድና ስራ አመራር ስልጠና መሰጠት ጀመረ
የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት በተቋሙ የአካዳሚክ አመራሮች የማቀድ ፣ የመምራት ፣ምዘናና ውሳኔ የመስጠት ክህሎታቸውን ለማሻሻል የሚያግዝ ተግባር ተኮር ስልጠና ሰኔ 7/2017 መሰጠት ጀምሯል።
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገየ የተቋማችን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት በአመራር ጥበብ የተገነባ መሪ ማፍራት የመጀመሪያ ስራችን በማድረግ አቅደን ወደ ስራ ገብተናል ብለዋል ፡፡ አያይዘውም ክህሎቱ የተገነባና ተቋሙን በባለቤትነት የሚመራ የሰው ሀይል ማፍራት ላይ አላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡
ስልጠናውን የሚያስተባብሩት የመምህራን ልማት አስተባባሪ መ/ር ወንድሙ በየነ በበኩላቸው በሁለት ዙር በሚሰጠው ስልጠና የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ዳይሬክተሮች እና አስተባባሪዎች እንደሚሳተፉ ገልፀው ስልጠናው ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ ለመወጣት ያስችላል ብለዋል ፡፡
ከአማራ ክልል ስራ አመራር አካዳሚ በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ስትራቴጀካዊ እቅድ፣ስራ አመራር ፣ ስራ አፈፃፀም እና የብቃት ምዘናን እንደሚዳስስ ለመረዳት ተችሏል ፡፡
ሰኔ 8/2017 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ