
የማህበረሰብ ውይይት ተካሄደ
የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ክፍል ኃላፊዎች፣የሰሜን ጎንደር ዞን፣ የደባርቅ ወረዳና ከተማ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው አዋሳኝ ቀበሌ አመራሮች ፣የሃይማኖት አባቶች፣የሃገር ሸማግሌዎች፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች በተገኙበት ግንቦት 1/2017 ዓ.ም የማህበረሰብ ውይይት ተካሄዷል::
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ


ዩኒቨርሲቲው በአዋጅ ተቋቁሞ ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመማር ማስተማር፣ ጥናትና የምርምር፣ በቴክኖሎጅ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ገልፀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ረገድ መልካምና አበረታች ጅምሮች መኖራቸውን አስታውሰዋል:: የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች ዋነኛ አላማ ከተቋሙ ባለቤት ከሆነው ህዝብ ጋር ቀጥተኛ ውይይት በማካሄድ እና መረጃ በመለዋወጥ በትኩረት የሚሰሩ ጉዳዮችን በመለየት የዕቅድ አካል አድርጎ ለመስራት ነው ብለዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ “የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ የምክክር መድረክ ” በሚል ርዕስ
በህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ በመ/ር አምሳሉ ተበጀ በቀረበው የውይይት መነሻ ጽሁፍ ዩኒቨርሲቲው ከምስረታው ጀምሮ በመማር ማስተማር፣ በመሰረተ ልማት፣ በዲጅታላይዜሽን እና አጋርነት ዙሪያ አሁን የደረሰበት አጠቃላይ እይታ፣ በትምህርት፣ በአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ ቴክኖሎጅ ሽግግር እና በግብርና ዘርፍ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ተግባራት ተዳሰዋል፡፡
በቀረበው ፅሁፍ እና ከማን ምን ይጠበቃል በሚል መነሻ ሀሳብ ከተሳታፊዎች በርካታ ገንቢ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ከታዳሚዎች በተሰጡት አስተያየቶች መሰረት የጤና ኮሌጅ እና ሌሎች ፉኩሊቲዎችን በማስፋፋት ተጨማሪ ካምፓሶችን ለመክፈት፣ሞዴል ማህበረሰባዊ እና አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት፣በተለይ ለአጎራባች ቀበሌዎች አቅም በፈቀደ መጠን የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለመዘርጋት፣በተጠና መንገድ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ተጨማሪ ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮችን ለማካሄድ፣የተጀመሩ የእውቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር፣የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል፣ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ከተጋረጡበት ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮዊ አደጋዎች ለማዳን በትኩረት እንደሚሰራ በከፍተኛ አመራሮች የማጠቃለያ አስተያየት መመላከቱን መገንዘብ ተችሏል፡፡
ግንቦት 02/2017 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
For the latest updates: